መፈክራችን ብር፣ ብር፣ ብር አሁንም ብር ነው !!!!
መፈክራችን ብር፣ ብር፣ ብር አሁንም ብር ነው !!!! ምርጫ ቦርድ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ጊዚያዊ እውቅና፣ ሙሉ እውቅና ለመስጠትና ሰነድ ለማሻሻል ( ለጊዚያዊ እውቅናና ሰነድ ለማሻሻል ክፍያ አልነበረም) ያስከፍል የነበረውን ከ200 ብር የማይበልጥ የአገልግሎት ዋጋ ወደ 30,000፣ 15, 000 እና 5000 ብር በድምሩ 50,000 ማድረጉን ባወጣው መግለጫ ገልጿል የመደራጀት፣ ሐሳብህን በተደራጀ መንገድ በነጻነት የመግለጽ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብትህ በገንዘብ እንደ ሸቀጥ ሲሸጥልህ ይህንን ይመስላል። የመደራጀት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት ሐብት ካላቸው ጥቂቶች ሐብት ወደ ሌላቸው ሁሉም ዜጎች ከወረደ በርካታ መቶ ዓመታት አልፎታል። ተደራጅተህ መብትህን ለመጠየቅና ታግለህ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብትህን ለማስከበር በሺህዎች የሚቆጠር ብር ክፍያ መጠየቅ ከተጀመረ ለምርጫ አገልግሎት፣ ለምርጫ ካርድ፣ የምርጫ ፓስተር ለመለጠፍያና የማስታወቂያና ቅስቀሳ ለማድረግ ክፍያ ላለመጠየቃችን እርግጠኛ መሆን አይቻልም።