የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ
የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ
ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ድርጅት አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በሱማሌ ክልል የገዢው ፓርቲ መዋቅር ተሳታፊዎችን የሚለይበትና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽ የሚያፍንበት ህገ-ወጥ አሰራር መዘርጋቱን የሚገልጸው ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ በምክክር መሳተፍ ረብ የለሽ ነው ሲልም ገልጾታል፡፡
ፓርቲው ከሱማሌ ክልል ውጪ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ሂደቱ ሊሳካ ይችላል ሲልም በጥያቄ መልስ አንስቷል፡፡
በቀጣይም ሁሉን አቀፍ የድርድር መድረክ እስካልተዘጋጀ ድረስ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይችልም ጠቁሟል፡፡
ኦብነግ በ2010 ዓ.ም ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ለማድረግ ከፌዴራሉ መንግስት ጋር ስምምነት አድርጎ መግባቱ አይዘነጋም፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ