የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ማብራሪያ ማቅረባቸውን አስታወቁ።
የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ማብራሪያ ማቅረባቸውን አስታወቁ። ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም እና የአማራ ፋኖ በጎንደር ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በስልክ ቆይታ አድርገዋል። በአማራ ማኅበር በአሜሪካ (AAA) አመቻችነት በተደረገው የሚዲያ ብሪፊንግ ተግባር፣ የፋኖ አመራሮቹ ከዋሽንግተን ፖስት (Washington post)፣ ሮይተርስ የዜና አገልግሎት (Reuters)፣ ዘኢኮኖሚስት (The Economist)፣ ብሉምበርግ (Bloomberg) እና ከአውሮፖ ፍሪላንስ (freelance journalist from Europe) ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል። በዚህም የፋኖ አመራሮቹ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ በተለይም የአብይ አህመድ ቡድን በንፁሃን ላይ እያደረገ ስላለው ጭፍጨፋ አጭር ገለፃ ካደረጉ በኋላ፣ በጋዜጠኞች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ እና ማብራሪያ እንደሰጡ ተገልጿል። በዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ እና የጦር ወንጀሎች ለማጣራት የውጭ ገለልተኛ ቡድን ገብተው ለማጣራት እንዲችሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ልታደርጉ ትቀበላላችሁ ወይ? የአማራ ክልልን ከዋና ዋና ከተሞች በስተቀር 90 በመቶ ተቆጣጥራችኋል ይባላል፣ ክልሉን ሙሉውን ብትቆጣጠሩ ምን ታደርጋላችሁ? እናንተ በምትቆጣጠሯቸው ቦታዎች ለህዝቡ ምን አይነት አገልግሎት እየሰጣችሁ ነው? እና መሰል ጥያቄወች ይገኙበታል። በተጨማሪም፣ እናንተ በተቆጣጠራችኋቸው ቦታዎች የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች፣ ለምሳሌ ዘረፋ እና እገታ የመሳሰሉትን እንዴት ነው የምትፈቱት? ህወሓት ከተከ...
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ