ልጥፎች

መፈክራችን ብር፣ ብር፣ ብር አሁንም ብር ነው !!!!

ምስል
  መፈክራችን ብር፣ ብር፣ ብር አሁንም ብር ነው !!!! ምርጫ ቦርድ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ጊዚያዊ እውቅና፣ ሙሉ እውቅና ለመስጠትና ሰነድ ለማሻሻል ( ለጊዚያዊ እውቅናና ሰነድ ለማሻሻል ክፍያ አልነበረም) ያስከፍል የነበረውን ከ200 ብር የማይበልጥ የአገልግሎት ዋጋ ወደ 30,000፣ 15, 000 እና 5000 ብር በድምሩ 50,000 ማድረጉን ባወጣው መግለጫ ገልጿል የመደራጀት፣ ሐሳብህን በተደራጀ መንገድ በነጻነት የመግለጽ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብትህ በገንዘብ እንደ ሸቀጥ ሲሸጥልህ ይህንን ይመስላል። የመደራጀት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት ሐብት ካላቸው ጥቂቶች ሐብት ወደ ሌላቸው ሁሉም ዜጎች ከወረደ በርካታ መቶ ዓመታት አልፎታል። ተደራጅተህ መብትህን ለመጠየቅና ታግለህ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብትህን ለማስከበር በሺህዎች የሚቆጠር ብር ክፍያ መጠየቅ ከተጀመረ ለምርጫ አገልግሎት፣ ለምርጫ ካርድ፣ የምርጫ ፓስተር ለመለጠፍያና የማስታወቂያና ቅስቀሳ ለማድረግ ክፍያ ላለመጠየቃችን እርግጠኛ መሆን አይቻልም።

የድሮን አዛዦች ቡድን መገኛ

  የድሮን አዛዦች ቡድን መገኛ ባ/ዳር ቀበሌ 13እና ቀበሌ 03 ኢመግሬሽን ጀርባ ስቨልሰርቪስ እና ሙሉዓለም አዳርሽ ጀርባ Ict ቢሮ ነው አንድ አማራ

የዘሜ መግለጫ ሌላ ፻ ተራሮች ኾኖ ውሏል ለካ

ምስል
  የዘሜ መግለጫ ሌላ ፻ ተራሮች ኾኖ ውሏል ለካ መግለጫው የረፈረፋቸው ሁሉ አረፋ ሲደፍቁ ውለዋልና። ጥቅምት ፲ ለማለት መስከረም ፲ መባሏ serious ማወናበጃ ተደርጋ የተንታኝ ዓይነት ሳይወራጭባት አልቀረም። ወሬአቸው በሦስት ነገሮች ይፈርሳል። ፩. የዘመነ ቃል የጊዜ ጥቁምታ (Time line) አለው። በመልእክቱ የተመስገን ጥሩነህን የጥቅምት ስብሰባ ያነሣል። ተመስገን "ዘመነን አስወግደነዋል - ከእንግዲህ ድምፁን አትሰሙትም" ብሎ ባሕር ዳር ለሰበሰባቸው ካድሬዎቹ የወሸከተው ጥቅምት ከባተ ነው። መቼስ የእናንተ ጉድ አያልቅም፤ "ዘሜ ነቢዩ በመስከረም ፲ ተመስገን ጥቅምት ላይ እንደዚህ ሊንዘባዘብ እንደሚችል ተነበየ" ልትሉ ይኾናል እኮ። ፪. መስከረም ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. ስለ ዘመቻ ፻ ተራሮች መግለጫ ሰጥቷል። ሞተ ተመታ ተያዘ ዓይነት ወሬ የመጣው ከተመስገን ጥሩነህ የጥቅምት ንግግር በኋላ ነው። መስከረም ፳፱ ላይ ሰሞኑን ስለዘመነ የተነዛው ኹሉ አልተባለም። እንዲያውም በመስከረም ፳፱ መግለጫው ለምን በቪድዮ አልመጣም በሚል "ቆስሏል" እያሉ የሐሰት ወሬ ነበረ ያናፈሱት። ዘመነን መስከረም ፲ ላይ የአኹኑን ዓይነት መግለጫ ለመስጠት በቂ ገፊ ምክንያት አልነበረም። እንኳን እርሱ ሊናገርበት ብልጽግናዎችም ገና አላሰቡበት። ፫. አኹን በማያወላዳ ኹኔታ በራሱ አንደበት መስከረም የሚለው በጥቅምት ፲ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. አርትዖት ተሰጥቶበታል።

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ

ምስል
  የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ድርጅት አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በሱማሌ ክልል የገዢው ፓርቲ መዋቅር ተሳታፊዎችን የሚለይበትና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽ የሚያፍንበት ህገ-ወጥ አሰራር መዘርጋቱን የሚገልጸው ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ በምክክር መሳተፍ ረብ የለሽ ነው ሲልም ገልጾታል፡፡ ይህ አግላይ አሰራር አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበትን አላማ የሚጥስ ነው ሲልም በምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ላይ ጥያቄ አንስቷል፡፡ ፓርቲው ከሱማሌ ክልል ውጪ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ሂደቱ ሊሳካ ይችላል ሲልም በጥያቄ መልስ አንስቷል፡፡ በቀጣይም ሁሉን አቀፍ የድርድር መድረክ እስካልተዘጋጀ ድረስ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይችልም ጠቁሟል፡፡ ኦብነግ በ2010 ዓ.ም ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ለማድረግ ከፌዴራሉ መንግስት ጋር ስምምነት አድርጎ መግባቱ አይዘነጋም፡፡

የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ማብራሪያ ማቅረባቸውን አስታወቁ።

ምስል
  የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ማብራሪያ ማቅረባቸውን አስታወቁ። ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም እና የአማራ ፋኖ በጎንደር ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በስልክ ቆይታ አድርገዋል። በአማራ ማኅበር በአሜሪካ (AAA) አመቻችነት በተደረገው የሚዲያ ብሪፊንግ ተግባር፣ የፋኖ አመራሮቹ ከዋሽንግተን ፖስት (Washington post)፣ ሮይተርስ የዜና አገልግሎት (Reuters)፣ ዘኢኮኖሚስት (The Economist)፣ ብሉምበርግ (Bloomberg) እና ከአውሮፖ ፍሪላንስ (freelance journalist from Europe) ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል። በዚህም የፋኖ አመራሮቹ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ በተለይም የአብይ አህመድ ቡድን በንፁሃን ላይ እያደረገ ስላለው ጭፍጨፋ አጭር ገለፃ ካደረጉ በኋላ፣ በጋዜጠኞች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ እና ማብራሪያ እንደሰጡ ተገልጿል። በዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ እና የጦር ወንጀሎች ለማጣራት የውጭ ገለልተኛ ቡድን ገብተው ለማጣራት እንዲችሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ልታደርጉ ትቀበላላችሁ ወይ? የአማራ ክልልን ከዋና ዋና ከተሞች በስተቀር 90 በመቶ ተቆጣጥራችኋል ይባላል፣ ክልሉን ሙሉውን ብትቆጣጠሩ ምን ታደርጋላችሁ? እናንተ በምትቆጣጠሯቸው ቦታዎች ለህዝቡ ምን አይነት አገልግሎት እየሰጣችሁ ነው? እና መሰል ጥያቄወች ይገኙበታል። በተጨማሪም፣ እናንተ በተቆጣጠራችኋቸው ቦታዎች የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች፣ ለምሳሌ ዘረፋ እና እገታ የመሳሰሉትን እንዴት ነው የምትፈቱት? ህወሓት ከተከ...

ሰበር ዜና - የአብይ አህመድ ልዩ ኦፕሬሽን ዝርዝር ደርሶናል

ምስል
  በአማራ ክልል ስለሚካሄደው የአብይ አህመድ ኦፕሬሽን ልዩ የሆነ ጥብቅ መረጃ ለንቃት ሚዲያ ደርሶታል። መረጃው ይህንን ንጹሃን እየተጨፈጨፉበት ያለውን የድሮን ጥቃት የተመለከተ ሚስጢራዊነቱ በጥቂት አመራሮች ብቻ የተያዘ ጥብቅ መረጃ ሲሆን ንቃት ሚዲያ ከሰዓታት በኋላ የሚያቀርበው ይሆናል። ሰበር ዜና - የአብይ አህመድ ልዩ ኦፕሬሽን ዝርዝር ደርሶናል

ዘንድሮ እንደ ዳንኤል ክብረት ስሙ የበዛለት የለም

ምስል
  ዘንድሮ እንደ ዳንኤል ክብረት ስሙ የበዛለት የለም። ዛሬም አዲስ ስም ወጥቶለታል። እሱም ዳኒ ጩለሌው ተብሏል። ከዚህ በፊት የነበሩት ስሞች፦ ዘንዘሪጡ ዳንኤል ጋኔል ክስረት ዳኒ ቦይ ሂሳቡ አሁን ደግሞ: ዲኒ ጩለሌው!